ጥር፣24/2013ዓ/ም፣ ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰንዳፋየሰላም ሚኒስቴር በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ለሚሰማሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ ወጣቶች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህ ስልጠና ላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 38 የአካል ብቃት አሰልጣኞችን በሀገሪቱ በሚገኙ 19 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በመላክ ከ29 ሺህ 900 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፣ የስነ-ምግባር መርሆች እንዲሁም ሌሎች ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሳዊ አካል ብቃት ተወካይ ዳይሬክተር የሆኑት ኢ/ር አድማሱ አላሮ እንደተናገሩት በሀገሪቱ ባሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና አሰልጣኞችን ከጥር 02/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ በመላክ ለ45 ተከታታይ ቀናት ስልጠናዎችን ፖሊሳዊ ዲሲፕሊን በጠበቀ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡