ጥር 21፣ 2013 ዓ.ም ፤ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሠንዳፋየጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱላሂ አብዱ ፈራህ እና የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የመረጃ ደህንነትና ኢምግሬሽን ሀላፊ ኮሎኔል አብዱልቃድር ኢብራሂም በቀን 21/05/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሪዚዳንት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ፣ምክትል ፕሬዝደንቶች እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጉብኝት አደረጉ፡፡ በጉብኝታቸውም ወቅት ስለ ዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ገፅታ ኢ/ር ጎሳዬ ታደሰ አጭር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙትን ቤተ-መፅሀፍትን፣ ቤተ-መዘክር እንዲሁም አዲስ የተገነባውን የዩኒቨርሲቲውን ግቢ(ካምፓስ) ጎብኝተዋል፡፡