ጥር 18/2013 ዓ.ም፤ ሰንዳፋ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ዕጩ መኮንኖች ባሳዩት መልካም ስነ-ምግባር፣ በነበራቸው የትምህርትና ስልጠና አፈፃፀም እና የትከሻ ምልክት መልበሻ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ 71 የ10ኛ ዙር ድህረ-ምረቃ ዲፕሎማ የሁለተኛ ዓመት የትክሻ ምልክት እንዲሁም 118 የ11ኛ ዙር ድህረ-ምረቃ ዲፕሎማ ዕጩ መኮንኖች የአንደኛ ዓመት የትክሻ ምልክት በአጠቃላይ 189 ዕጩ መኮንኖች ለዚህ ፕሮግራም በቅተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ፣ ም/ፕሬዝዳንቶች፣ የየትምህርት ስልጠና ክፍል ዳይሬክተሮች፣ ሌሎች አመራሮችና መምህራን ተገኝተዋል፡፡በመጨረሻም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ለዕጩ መኮንኖች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት እና የስራ መምሪያ ያስተላለፉ ሲሆን “በመልካም ስነምግባራችሁ እና በትምህርትና ስልጠና አፈፃፀማችሁ ዛሬ የወሰዳችሁት የትከሻ ምልክት በቀጣይ ወደ ማህበረሰቡ በመግባት ለማገልገል ለሚሰጣችሁ ተልዕኮ እና ሀላፊነት የምትዘጋጁበት በመሆኑ እና ለሌሎችም አርዓያ የምትሆኑበት በመሆኑ ተግታችሁ መስራት አለባችሁ” ሲሉ አሳስበዋል፡፡