በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የፖሊስ ጥናት ሲምፖዚየም ተጀመረ

ሀምሌ 8/2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ፤በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከሀምሌ 8 እስከ 9/2013 ዓ.ም የሚቆይ 3ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ጥናት ሲፖዚየም እየተካሔደ ነው፡፡በተዘጋጀው የፖሊስ ጥናት ሲፖዚየም የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፣የፌደራል ፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ፣ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ሙህራኖች እና ጥናት አቅራቢዎች እየተሳተፉ ነው፡፡እዬተካሄደ ባለው ሲፖዚየም 15 ችግር ፈች የጥናትና ምርምር ውጤቶች እንደሚቀርቡ እና ከነዚህም ውስጥ 4ቱ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ምሁራን እንደሚቀርቡ ተገልፀዓል፡፡በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ም/ኮሚሽነር መስፍን አበበ አንጋፋው ተቋማችን ብቁ የፖሊስ መኮንኖችን እንዲያፈራ ታስቦ በኮሌጅነት ከተመሰረተ 75 አመታችንን ልንይዝ ሶስት ወራት ብቻ የቀሩት ተቋማችን የረጅም አመታት አገልግሎታችን እና ዕድገታችንን በመፈተሽ በፖሊስ ዘርፉ ያሉ አፈፃፀሞችን ውጤታማነትና ጉድለቶችን የምናይበት ጥናትና ምርምሮችን በማካሔድ የዘርፉን እድገት ቀጣይነት ማረጋገጥ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን በማስገንዘብ 3ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ጥናት ሲፖዚየም በይፋ መከፈቱን አብስረዋል፡፡ በዚሁም አያይዘው ኮሚሽነሩ “እኛ ፖሊሶች በሰባዊነት እናገለግላለን በጀግንነት እንጠብቃለን !! ” እናንተም ከጎናችን ሆናችሁ በመተባበር ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡